ግለሰብና የቤተሰብ አባላት

የጡሮታ ሱፐርአኑዌሽንን ቀድሞ ማውጣት

ለሚፈቀድላቸው ግለሰቦች ማመልከት የሚችሉት ኦንላይን መስመር በ myGov አድርጎ እስከ $10,000 ዶላር ከጥጡታ ሱፐራኑዌሽን ከቀን 31 ታህሳስ/December 2020 ዓ.ም በፊት ለማግኘት ማመልከት ይችላሉ።

ያለዎትን ሱፐር ቀደም ብሎ መጠቀሙ በሚኖርዎት ሱፐር ሚዛናዊ መጠን ችግር እንደሚያመጣና ለወደፊት ባለዎት የጡሮታ ገቢ መጠን ላይ ችግር ሊያስከስት ይችል ይሆናል። ያለዎትን ሱፐር ቀደም ብሎ ለማውጣት ከማመልከትዎ በፊት የፋይናሻል ባለሙያን ምክር ግምት ውስጥ ማስገባት። .

ስለ ሱፐርን አስቀድሞ ማውጣት የበለጠ መረጃ ብበድረገጽ፡ www.ato.gov.au/early-access ላይ ይገኛል ወይም ከአውስትራሊያ መገበሪያ ቢሮ (ATO) ጋር ለመነጋገር፤ ለትርጉምና አስተርጓሚ አገልግሎት (TIS National) በስልክ 13 14 50 አድርጎ መደወል።

ማስወጣት የለም

በአስተዳደር ግዛት እና በተሪቶርይ መንግሥታት መባረሩ  ለስድስተ ወራት እንዲቆይ ተደርጓል። የንብረት ባለንብረቶችና ተከራዮች ስለ አጭር ጊዜ ኩንትራት ስምምነት እንዲነጋገሩ ይደገፋል። እርስዎን ከሚወክል አስተዳደር ግዛት ወይም ተሪቶርይ መንግሥት ጋር ለበለጠ ዝርዝር መረጃ ማጣራት።

ለጡረተኞች አነስተኛ መጠን ለማውጣት ምርጫዎች

አነስተኛ መጠን ማውጣት ፍላጎት ላላቸው ጡሮተኞችና እና ተመሳሳይ ምርት ላላቸውና የገቢ መጠናቸው በ 50% እጂ የቀነሰ አካውንት ላላቸው በ2019-20 እና 2020-21 ዓ.ም ባለው ጊዜ ለመርዳት በ COVID-19 ወረርሽን ሳቢያ ተገቢ የሆነ ኪሳራና በፋይናሻል ገብያዎች የተዳከሙትን መርዳት ይሆናል።

የበለጠ መረጃ ለማግኘት በድረገጽ፡ www.ato.gov.au/drawdown ላይ ገብቶ ማየት።

ለሥራ ቀጣይ ክፍያ

የሥራ ቀጣይ ክፍያ የሚረዳው ለንግድ ሥራዎች ሲሆን በኮቪድ/ COVID-19 ችግር ምክንያት ለተቀጣሪዎች ደመወዝ መክፈል ላቃታቸው እርዳታ ይሆናል። አውስትራሊያኖች ብዙዎች ሥራዎች እንዳሉና ገቢ ማግኘቱም ቀጥሏል።.

የርስዎ ቀጣሪ እርስዎን ወክሎ በየሁለት ሳምንት ለሥራ ቀጣይ ክፍያ ማመልከት ከፈለጉ ለርስዎ ያሳውቃል።

ለበለጠ መረጃ በድረገጽ ማየት፤ www.ato.gov.au/jobkeeper

የአሰራር ዘዴ ደህንነትና ተገቢነት ስለመጠበቅ

ከ COVID-19 ቫይረስ እና ሌሎች ማጭበርበሮች ጋር ያተኮረ በአውስትራሊያኖች ላይ ያተኮረ ነው። በኢሜል፤ SMS ወይም በስልክ ጥሪ ማጭበበሪያዎች ወይም አጠራጣሪዎች ጋር ግንኙነት ስለማድረግ ካሰቡ መጀመሪያ ከእኛ ጋር ማጣራት።

የአውስትራሊያ ግብር ቢሮ/ATO ያካሄደው ድርጊት ትክክለኛ ሰለመሆኑ እርግጠኛ ካልሆኑ፤ መልስ አለመስጠት። ለ ATO የማጭበርበር ሆትላይን መስመር በስልክ 1800 008 540 መደወል ወይም በድረገጽ፡ www.ato.gov.au/scams ላይ ማየት።

የሆነ ሰው ለርስዎ የማንነት መለያ መረጃ ሰርቋል ወይም አላግባብ ተጠቅሟል ብለው ካሰቡ እንረዳዎታለን። ለግብር ከፋዮች ያላቸውን የግብር መለያ መረጃን እንደገና እንዲያቀናጁ ለመርዳት መረጃን፤ ምክርንና ድጋፍ እናቀርባለን።

  • እንዲሁም እርስዎና ግለሰብ ወይም ንግድ ሥራዎት በትክክለኛ ነገር ላይ እንደማይካሄድ ለእኛ ማሳወቅ ይችላሉ፤ በድረገጽ፡ www.ato.gov.au/tipoff

የመንግሥት ክፍያዎችና አገልግሎቶች

የመንግሥት ክፍያዎችና አገልግሎቶች ለሴንተርሊንክ ክፍያ ባያገኙም የአገልግሎቶች አውስትራሊያ ሊረዳዎት ይችል ይሆናል። ወደ አገልግሎት መስጫ ማእከል መሄድ አያስፈልግዎም። በአማራጭነት በራስ መገልገያን መጠቀም ይችላሉ። እንዲሁም ለማሕበራዊ ሰራተኛ ማግኘት ይችላሉ። ቀደም ሲል ደንበኛ ከሆኑ፤ በኮቪድ/(COVID-19) ቫይረስ ምክንያት. በእኛ ክፍያዎችና አገልግሎቶች ላይ ለውጦች እንዳሉ ነው። በተለያዩ ቋንቋዎች የበለጠ መረጃ ለማግኘት በድረገጽ፤ servicesaustralia.gov.au/covid19 ላይ ገብቶ ማየት።