ለግለሰቦችና ቤተሰብ አባላት

ማስወጣት የለም

በአስተዳደር ግዛት እና በተሪቶርይ መንግሥታት መባረሩ  ለስድስተ ወራት እንዲቆይ ተደርጓል። የንብረት ባለንብረቶችና ተከራዮች ስለ አጭር ጊዜ ኩንትራት ስምምነት እንዲነጋገሩ ይደገፋል። እርስዎን ከሚወክል አስተዳደር ግዛት ወይም ተሪቶርይ መንግሥት ጋር ለበለጠ ዝርዝር መረጃ ማጣራት።

ለጡረተኞች አነስተኛ መጠን ለማውጣት ምርጫዎች

አነስተኛ መጠን ማውጣት ፍላጎት ላላቸው ጡሮተኞችና እና ተመሳሳይ ምርት ላላቸውና የገቢ መጠናቸው በ 50% እጂ የቀነሰ አካውንት ላላቸው በ2019-20 እና 2020-21 ዓ.ም ባለው ጊዜ ለመርዳት በ COVID-19 ወረርሽን ሳቢያ ተገቢ የሆነ ኪሳራና በፋይናሻል ገብያዎች የተዳከሙትን መርዳት ይሆናል።

የበለጠ መረጃ ለማግኘት በድረገጽ፡ www.ato.gov.au/drawdown ላይ ገብቶ ማየት።

ለሥራ ቀጣይ ክፍያ

የመንግሥት ሥራ ቀጣይ ክፍያ በኮቪድ/ COVID-19 ችግር ለደረሰባቸው የንግድ ሥራዎች ጊዚያዊ መደጎሚያ ክፍያ እንደነበር ነው።

ፈቃድ ያላቸው ቀጣሪዎች፤ የብቸኛ ነጋዴዎች እና ሌሎች ድርጅቶች ለሚፈቀድላቸው ተቀጣሪዎች የሚሆን ለሥራ ቀጣይ ክፍያዎች ለማግኘት ማመልከት ይችሉ እንደነበር። ይህ በግብር ቢሮ/ATO በኩል በየወሩ ላልተክፈለ ለቀጣሪው ይሰጥ ነበር።

የንግድ ሥራዎች ለሥራ ቀጣይ ክፍያ በ ATO's የንግድ ሥራ መግቢያ/Business Portal በኩል መመዝገብ ይችላሉ። የራስዎ ንግድ ወይም በግብር ታክስ ወይም በ BAS ድርጅት ተመዘገቦ ከነበር በሆት ላይን መስመር myGov መጠቀም ነው። ’

ስለ የሥራ ቀጣይ ክፍያ የቀረበን መረጃ ለማግኘት በድረገጽ www.ato.gov.au/JobKeeper ላይ ገብቶ ማየት።

ለሥራ ፈጣሪ የመቅጠሪያ ወጪ ክፍያ

የሥራ ፈጣሪ መቅጠሪያ ወጪ ክፍያ አሰራር እድሚያቸው ከ16 እስከ 35 ዓመት ለሆኑ ሥራ ፈላጊዎች የንግድ ሥራዎች ለመቅጠር የሚደረግ ማበረታቻ ነው።

የተፈቀደለትን ተጨማሪ ተቀጣሪዎችን በቀን 7 ጥቅምት/October 2020 እና ቀን 6 ጥቅምት/October 2021 ዓ.ም ባለው ጊዜ ለመቅጠር ለሥራ ፈጣሪ መቅጠሪያ ወጪ ክፍያ የተፈቀደላቸው ቀጣሪዎች ማግኘት ይችላሉ።

ለበለጠ መረጃ በድረገጽ፤ www.ato.gov.au/jobmakerhiringcredit ላይ ገብቶ ማየት።

የአሰራር ዘዴ ደህንነትና ተገቢነት ስለመጠበቅ

ገንዘብ በሚከፍሉበት ጊዜ ወይም የርስዎን ግላዊ መረጃ በሚሰጡበት ጊዜ በተጭበረበረ መልኩ እ3ንዳይሆን መሞከር።

አጭበርባሪዎች ከታማኝ ድርጅቶች እንደሆኑ፤ እንደ የአውስትራሊያ ግብር ቢሮ/ATO ያስመስላሉ። የአውስትራሊያ ግብር ቢሮ/ATO ያካሄደው ድርጊት ትክክለኛ ሰለመሆኑ እርግጠኛ ካልሆኑ፤ መልስ አለመስጠት። ለ ATO የማጭበርበር ሆትላይን መስመር በስልክ 1800 008 540 መደወል ወይም በድረገጽ፡ www.ato.gov.au/scams ላይ ማየት ይችላሉ።

የመንግሥት ክፍያዎችና አገልግሎቶች

የመንግሥት ክፍያዎችና አገልግሎቶች ለሴንተርሊንክ ክፍያ ባያገኙም የአገልግሎቶች አውስትራሊያ ሊረዳዎት ይችል ይሆናል። ወደ አገልግሎት መስጫ ማእከል መሄድ አያስፈልግዎም። በአማራጭነት በራስ መገልገያን መጠቀም ይችላሉ። እንዲሁም ለማሕበራዊ ሰራተኛ ማግኘት ይችላሉ። ቀደም ሲል ደንበኛ ከሆኑ፤ በኮቪድ/(COVID-19) ቫይረስ ምክንያት. በእኛ ክፍያዎችና አገልግሎቶች ላይ ለውጦች እንዳሉ ነው። በተለያዩ ቋንቋዎች የበለጠ መረጃ ለማግኘት በድረገጽ፤ servicesaustralia.gov.au/covid19 ላይ ገብቶ ማየት።