ለንግድ ሥራዎች

ሥራ ቀጣይ ክፍያ

የመንግሥት ሥራ ቀጣይ ክፍያ ጊዜያዊ የድጎማ ክፍያ ሲሆን በኮሮና ቫይረስ (COVID-19) ሳቢያ ችግር ለደረሰባቸው የንግድ ሥራዎች ጊዜያዊ የሚሰጥ ክፍያ እንደነበር ነው።

የሚፈቀድላቸው ቀጣሪዎች፤ የግል ነጋዴዎች እና ሌሎች ማግኘት የሚችሉት ፈቃድ ላላቸው ተቀጣሪዎች የሥራ ቀጣይ ክፍያዎችን ማመልከት ይችሉ ነበር። ይህ ክፍያ በ ATO በኩል የሚሰጠው ለቀጣሪው በቅድሚያ በየወሩ ይሰጥ ነበር።

የንግድ ሥራዎች ለሥራ ቀጣይ ክፍያ በ ATO's የንግድ ሥራ መግቢያ/Business Portal በኩል መመዝገብ ይችላሉ። የራስዎ ንግድ ወይም በግብር ታክስ ወይም በ BAS ድርጅት ተመዘግበው ከነበረ ATO online services በሆት ላይን መስመር myGov መጠቀም ነው። ’

ለሥራ ቀጣይ ክፍያ መረጃ ለማግኘት በድረገጽ www.ato.gov.au/JobKeeper ላይ ገብቶ ማየት።  .

የፍጆታ ክፍያንና ደመወዝን ለመክፈል በጥሬ ገንዘብ እንቅስቃሴን ስለማረጋገጥ

ለሚፈቀድላቸው የንግድ ሥራዎችና አትራፊ ላልሆኑ (NFP) ድርጅቶች ለተቀጠሩ ሰራተኞች ከ$20,000 እስከ $100,000 በጥሬ ገንዘብ እንቅስቃሴ ማግኘት ሲችሉ ይህም የእንቅስቃሴ ገቢ መጠን መግለጫ ጽሁፍ ከመጋቢት/ March 2020 ዓ.ም እስከ መስከረም/ September 2020 ዓ.ም በየወሩ እና በየሶስት ወሩ በማስገባት ይሆናል።

የበለጠ ለማግኘት:

ለሙያ ስልጠና ተማሪና አሰልጣኞች

የአስትራሊያን በሙያ ብቃት ያለው ሥራ ቡድን በቀጣይነት ለማጠናከር መንግሥት እየረዳ ስለሆነ ታዲያ ፈቃድ ላላቸው የንግድ ሥራዎች ለሙያ ስልጠና ተማሪዎች እና አሰልጣኞች ለማስቀጠል ደመወዝ ከመቶ 50 እጅ ደመወዝ መደጎሚያ እስከ $21,000 ዶላር በማቅረብ ይሆናል።

የበለጠ መረጃ ለማግኘት:

ዱቤና ብድር

አዲስ ኮሮና ቫይረስ SME ዋስትና አሰራር ዘዴ ማለት በመጪው ወራት ላይ እርስዎን ለመርዳት ከተሳታፊ የሆኑ አበዳሪዎች ተጨማሪ ብድር ማግኘት ይችሉ ይሆናል።

በሥራ ካፒታል ወጪ የሚጠቅም አዲስ ደህንነቱ ላልተጠበቀ ብድሮች መንግሥት ከመቶ 50 እጅ ለSME አበዳሪዎች በመስጠት ዋስትና ያቀርባል።

እንዲሁም ሃላፊነት ካለው የማበደር ግዴታ በአበዳሪው አሁን ላሉት ትናንሽ የንግድ ሥራ ደንበኞች ዱቤ ስለማቅረብ መንግሥት ነጻ አድርጎታል።

ይህ ነጻ የመሆን ለስድስት ወራት እንደሆነና ከንግድ ሥራ ጋር ለተዛመዱ ማንኛውም ብድር ሲሆን፤ በዚህ የሚካተት አዲስ ብድር፤ በብድር መጠን የጨመረ እና የብድር መቀያየርና እንደገና ማቀናጀት ይሆናል።

ክልሎችንና ክፍሎችን ስለመርዳት

በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ሳቢያ ችግር ላጋጠማቸው ማህበረሰባት፤ ክልሎችና ኢንዱስትሪዎች ለመርዳት መንግሥት $1 ሚሊዮን ዶላር አቀናጅቷል። እነዚህ የገንዘብ እርዳታዎች የሚቀርቡት በወረርሽኝ ጊዜ እርዳታዎችን በመስጠት ለችግሩ ማገገሚያ እንዲረዳ ነው። በተጨማሪም፤ መንግሥት ለእኛ አየር መንገድ ኢንዱስትሪ እስከ $715 ሚሊዮን ዶላር በማቅረብ ይረዳል።

ለንግድ ሥራዎች ድጋፍ በሥራ ፈጣሪ እቅድ ጊዜያዊ እርምጃዎች

እንደ 2020–21 ዓ.ም ባጀት አንድ አካል መሆን የንግድ ሥራዎች ከኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ (COVID-19) ችግር ለመርዳት መንግሥት የተለያዩ እርምጃዎችን ለማካሄድ ነው።

እነዚህ እርምጃዎች ለግብር ቅናሽ ዋጋ፤ ቅነሳና ከማመልከት ጋር የተያያዘ እና በግብር ጊዜ የንበቶችን ዋጋ መውረድ ጋር ይዛመዳል። በ 2020–21 ዓ.ም እና በ 2021–22 ፋይናሻል ዓመታት በኮቪድ/ COVID-19 ሳቢያ የኢኮኖሚ ችግር ላጋጠማቸው የንግድ ሥራዎች ይረዳሉ።

በነዚህ እርምጃዎች የሚካተት:

  • ለሥራ ፈጣሪ መቅጠሪያ ወጪ ክፍያ
  • ጊዜያዊ ሙሉ ውጪውን
  • ለመመለስ ላቃታቸው
  • የንግድ ሥራን ኢንቨስትመንት መመለስ – የዋጋ መውረድን ማፋጠን
  • በቀጥታ ንብረት ማስወገድ
  • የትናንሽ ንግድ ሥራን ወድነበረበት እንዲመለስ ማፋጠን ይሆናል።