ስለ ኮሮና ቫይረስ/Coronavirus (COVID-19) እምነትና የተሳሳተ መረጃ

በኮቪድ/COVID-19 ክትባት የተሳሳተ መረጃ

የተሳሳተ መረጃ: ኮቪድ/COVID-19 ክትባቶች አደገኛ እንደሆኑና በውጭ አገር ላገኙት ሰዎች ከባድ ችግር እንደፈጠረ ነው።

እውነቱ: በአውስትራሊያ ውስጥ ክትባቶችን ለመጠቀም በህክምና ጥራት አስተዳደር/Therapeutic Goods Administration (TGA ) በኩል ተቀባይነት ያገኙ ናቸው። በአውስትራሊያ ውስጥ ክትባቶችን ከመጠቀም በፊት ተቀባይነት እንዲያገኙ በክትባቶች ደህንነት ላይ ጥልቀት ያለው ምርመራ ይካሄዳል። በዚህ የሚካተተው ጥንቃቄ በተሞላበት የክሊኒካል ሙከራ ጥናት በተገኘ ጥሬ መረጃ፤ ንጥረ ነገሮች፤ ኬሚስትሪ፤ ማምረትና ሌላ ነገሮችን ያካትታል። ስለ ኮቪድ/COVID-19 ክትባቶች መረጃ በ TGA’s ድረገጽ https://www.tga.gov.au/covid-19-vaccines ላይ ሊገኝ ይችላል።

በተጨማሪም በአውስትራሊያ ውስጥ ክትባቱ ከተሰጠ በኋላ ደህንነቱን ለማረጋገጥ በእያንዳንዱ ኮቪድ/COVID-19 ክትባት የሥራ ጥምረት ላይ የህክምና ጥራት አስተዳደር/ TGA በክትባቶች ላይ ቁጥጥር ያካሂዳል። እንዲሁም መንግሥት በውጭ አገር ያለን የበሽታ መከላከል ክትባት ፕሮግራም፤ በዩናይትድ ኪንግደም/UK፤ ጀርመንንና ኖርዋይን ያካተተ በቅርበት ሆኖ ይከታተላል። የነዚህ መረጃዎች በጋራ ሆነው ለአውስትራሊያኖች ደህንነቱ የተጠበቀና ተግባራዊ ለሆነ ኮቪድ/COVID-19 ክትባት ለማግኘት ይረዳል።

ክትባት ከወሰዱ በኋላ ችግር ካጋጠምዎት፤ ከጤና ባለሙያ እርዳታ ከፈለጉ እና ይህን ሪፖርት ለTGA በስልክ (1300 134 237) ማድረግ።

የተሳሳተ መረጃ: በኮቪድ/COVID-19 ቫይረስ ከሚሞቱ ሰዎች ክትባት በመውሰድ የሚፈጠር አንጻራዊ ችግር የሚሞቱ የሰዎ ቁጥር ይበዛል።

እውነቱ: ማንኛውም ክትባት አንዳንድ መካከለኛ የሆነ ችግሮች ሊፈጠሩ ይችላሉ። ከክትባቶች ጋር የሚፈጠሩት ዋና ችግሮች መርፌውን በተወጉበት ቦታ ላይ አንዳንድ ህመሞች፤ የመቅላት ወይም የማበጥ ችግሮች፤ የራስ ምታት ወይም መካከለኛ የሆነ ትኩሳትና ከፍተኛ የድካም መንፈስ ይሆናል። እነዚህ በአብዛኞቹ አንዳንድ የሀመም ማስታገሻ መሃኒት በመውሰድ መቆጣጠር ሲቻል በክንድ ላይ ችግር አይፈጥርም።

የህክምና ጥራት አስተዳደር/TGA – የአውስትራሊያ ህክምና ተቆጣጣሪ – ደህንነቱ ላልተጠበቀና ተግባራዊ ላልሆኑ ክትባቶች ተቀባይነት አይሰጡም። በቅርበት ሆነው ከሚከታተሉት ነገሮች አንዱ ለሚፈጠር ከፍተኛ የህመም ችግርን ነው።

አውስትራሊያ በዓለም ውስጥ በጣም ጥሩ ተቀባይነት ያለው የአሰራር ሂደት እንዳላት እና ከፍተኛ አንጻራዊ ችግር ለሚያስከስት ማንኛውም መድሃኒት በዚህ ሃገር ተቀባይነት አይሰጠውም። የ TGA’s ሥራ ከተቀባይነት መስጠት ጋር አያቆምም። እንዲሁም ከውጭ አገር ለሚመጡ ጥሬ መረጃ እና በዚህ የመዳረስ ሁኔታ ላይ በቅርበት ይከታተላሉ። ምንም የቀረ እድል የለም።

ከክትባት ጋር በተዛመደ ችግር ካጋጠምዎት፤ ከጤና ባለሙያ እርዳታ ከፈለጉ እና ይህን ሪፖርት ለTGA ለማድረግ በስልክ (1300 134 237) መደወል።

የተሳሳተ መረጃ: መንግሥት ክትባት ማዳረስ ለመጠቀም በሚል ሽፋን የርስዎን DNA ለመውሰድ ነው።

እውነቱ: ክትባቶች የሚወጉት በስውነትዎ ውስጥ ሲሆን ምንም ነገር ከሰውነትዎ የሚወጣ እንደሌለ እና ከርስዎ DNA ጋር የተዛመደ ነገር አይኖርም። አንዳንድ አዳዲስ ኮቪድ/COVID-19 ክትባቶች ለሰውነትዎ ከኮቪድ/ COVID-19 ጋር ለመታገል እንዲቋቋም የተበጣጠሰ መልእክተኛን RNA (mRNA) እንደሚጠቀም ለሰውነትዎ መመሪያ መስጠት ይሆናል። የ mRNA ክርስዎ DNA ጋር የሚያደርገው ምንም ነገር እንደሌለ ነው።

የተሳሳተ መረጃ: ቫይረሱ በፍጥነት ስለሚለወጥ ክትባቱ ምንም አይሰራም።

እውነቱ: ሁሉም ቫይረሶች ይለወጣሉ። ያላቸው ተፈጥሯዊ ለውጥ የተለመደ አካል እንደሆነና ኮቪድ/ COVID-19 የተለየ አይደለም። በማስረጃ በተረጋገጠው መሰረት የኮቪድ/COVID-19 ክትባቶች አሁንም በአዳዲስ ዝርያዎች ላይ ጥሩ እንደሚሰሩ ነው።

ይህ ማለት ሰዎች ተጨማሪ መድሃኒቶች ለመውሰድ ወይም እንደገና ክትባቱን መውሰድ ይኖርባቸዋል – ልክ እንደ ኢንፍሉዌንዛ/ፍሉ ክትባት።

አውስትራሊያ ውስጥ ለመጠቀም በአሁን ጊዜ ተቀባይነት ያገኙት ክትባቶች በኮቪድ/ COVID-19 ለሚከሰቱ ከባድ ህመሞችን በመከላከል ከፍተኛ ውጤት አሳይተዋል።

የተሳሳተ መረጃ: ኮቪድ/COVID-19 ለነበራቸውና ለዳኑ ሰዎች ክትባት መውሰድ አይኖርባቸውም።

እውነቱ: አንድ ሰው ከኮቪድ/COVID-19 የመከላከል ሀይላቸው ከሰው ወደ ሰው ይለያያል። ምክንያቱም ይህ ቫይረስ አዲስ ስለሆነ፤ ማንኛውም የተፈጥሮ በሽታ መቋቋሚያ ሀይል ለምን ያህል እንደሚቆይ ስለማናውቅ ነው። ኮቪድ/COVID-19 ቫይረስ ቢኖርብዎትም፤ አሁንም በሚችሉበት ጊዜ የኮቪድ/COVID-19 ክትባትን መውሰድ አለብዎት።

የተሳሳተ መረጃ: የኮቪድ/COVID-19 ክትባት ሶፍትዋር/ማይክሮቺፕስ እንዳለውና ለመቆጣጠር ይጠቅማል

እውነቱ: የኮቪድ/COVID-19 ክትባቶች ምንም ሶፍትዋር/ማይክሮቺፕስ የላቸውም።

ሌላ በኮቪድ/COVID-19 የተሳሳተ መረጃ

ትረታ/MYTH: ህጻናት ለኮቪድ/ COVID-19 ቫይረስ ‘ዋና አሰራጭ’ ናቸው

እውነቱ:  ታዳጊ ህጻናት በአጠቃላይ ለጀርሞችና ትላትል፤ ማለት እንደ ኢንፍሉወንዛ ‘ዋና አሰራጭ’ ናቸው ተብሎ ቢታወቅም ነገር ግን በአሁን ጊዜ ያለው ማስረጃ እንደሚለው የኮቪድ/ COVID-19 ቫይረስ በትምህርት ቤት ውስጥ ከህጻን ወደ ህጻን መተላለፉ ያልተለመደ ነው። በተጨማሪም በዓለም ውስጥ የትም ቦታ ይህ ቫይረስ በታዳጊ ህጻናት ላይ ከባድ ስርጭት ስለመፈጠሩ የሚያሳይ ጥሬ መረጃ እንደሌለ ነው። ምንም እንኳን ሊፈጠር ቢችልም፡ በአሁን ጊዜ ያለው ማስረጃ ግን ለኮቪድ/ COVID-19 ምክንያት የሆነ ህጻናት የቫይረሱ ዋና አሰራጭ እንዳልሆኑ ነው።

የተሳሳተ መረጃ:: አውስትራሊያ በቂ መሳሪያና አቅርቦቶች (ንጹህ አየር ማስገቢያ መሳሪያዎች/ventilators, ጭምብሎች፤ የምርመራ ማካሄጃ እቃዎች) ማግኘት አልቻለችም

እውነቱ:  አውስትራሊያ ጠመዝማዛን በማቃናት በጣም ጥሩ ውጤት እንዳላት፤ ይህም በእኛ ሆስፒታሎች ላይ የሚጨምረውን ችግር ግፊት አስወግደናል። 

በአውስትራሊያ ውስጥ ብዙ የግላዊ መከላከያ መሳሪያዎች ሲቀርብ ብዙዎቹ አውስትራሊያ ውስጥ የተመረቱ እና ሁልጊዜ ወደ አውስትራሊያ የሚላኩ ናቸው። ለምሳሌ፡ የአገር አቀፍ ህክምና ለመጠባበቂያ የተከማቸው በጥሩ እንዳለ እና በ2021 ዓ.ም ውስጥ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ የፊት መሸፈኛ ጭምብሎች መከላከያ ይቀርባል።  

ለአውስትራሊያ መንግሥት የመማክርት ኮሚቴዎች፤ ይህም በአውስትራሊያ ለተላላፊ በሽታ አሰራር መርበብ እና ህዝባዊ ጤና ጥበቃ ላቦራቶሪ አሰራር መርበብ ያካተተ ስለ ኮቪድ/ COVID-19 ምርመራ ማድረግ አስፈላጊነት በተደጋጋሚ መመሪያውን እንደገና በመገምገም፤ ለኮቪድ/ COVID-19 ቫይረስ ወረርሽኝ በሚካሄደው ጠቃሚ ምርመራ ለእኛ ህዝባዊ ጤና ጥበቃ ምላሽ እንደረዳ ለማረጋገጥ ነው።

የተሳሳተ መረጃ: በኮቪድ/COVID-19 ምክንያት ከጨመረው ጥያቄ ጋር የአውስትራሊያ ሆስፒታሎች ሊወጡት አልቻሉም

እውነቱ:  አውስትራሊያ የተስፋፋውን በመቆየር በጣም ጥሩ ውጤት እንዳመጣ፤ ይህ ማለት በእኛ ሆስፒታል ላይ ያለን የጫና መጨመር አስወግደናል። አውስትራሊያ በዓለም ደረጃ የጤና ጥበቃ አሰራር ዘዴ እንዳላት፤ ይህም በኮቪድ/COVID-19 ቫይረስ ወረርሽኝ ጊዜ አስፈላጊ ለሆኑ ተጨማሪ ጥያቄዎች ለማሟላት በደንብ ተቀምጧል። በዚህ የሚካተት በአውስትራሊያ መንግሥት፤ አስተዳደር ግዛት እና ተሪቶርይ መንግሥታት እንዲሁም የግል ጤና ጥበቃ ተቋም መካከል በጋርዮሽ ተጨማሪ የሆስፒታል አልጋዎች፤ የህክምና መሳሪያዎች፤ አቅርቦቶች እና የህክምና ባለሙያዎችን ነው።

የተሳሳተ መረጃ: የሁለት ሳምንት እንዳይወጡ መዘጋት ለኮቪድ/COVID-19 ቫይረስ ስርጭት ያቆማል

እውነቱ ለሁለት ወይም ሶስት ሳምንታት እገዳዎችን ማስገደድና ማንሳት እንዲሁም ወደ መደበኛ ህይወታችን መመለሱ የኮቪድ/COVID-19 ቫይረስ ስርጭትን አያቆመውም።

ከኮቪድ/COVID-19 ቫይረስ ጋር ያሉት አብዛኞቹ አነስተኛ የሆነ ብቻ ወይም ምንም ዓይነት የበሽታ ምልክቶች አይኖራቸውም። ለሁለት ሳምንታት ብቻ እገዳዎች የሚያመጣው ችግር የኮቪድ/COVID-19 ቫይረስ እያለባቸው ምልክት በማያሳዩ ሰዎች እገዳው ከተነሳ በኋላ ባለማወቅ ሌሎች ሰዎች በቫይረሱ ሊጋለጡ ይችላሉ።   

የኮቪድ/COVID-19 ቫይረስ ስርጭት ለማዳከም የሚረዳ በጣም ጥሩ የሆነው መንገድ እጅን መታጠብና የመተንፈሻን ጽዳት/ሃይጅን መጠበቅ፤ የአካል እርቀትን መጠበቅ፤ ድህና ካልሆኑ ምርመራ ማካሄድና እቤት መቆየት፤ እንዲሁም በማህበረሰብ መተላለፊያ ቦታ ላይ የአካል እርቀትን መጠበቅ በእርቀት የማይቻልበት ቦታ ላይ የፊት መሸፈኛ ጭምብልን በማጥለቅ ነው።

በአውስትራሊያ ውስጥ እና የመሰራጨት ሂደት በሚካሄድበት ቦታ ላይ የእኛ ጤና ጥበቃ ኤክስፐርቶች በቀጣይነት ብዛት ያለው አዳዲስ ጕዳዮችን እንደሚቆጣጠሩ ነው። ከዚያም ማንኛውንም አዲስ ደንብ ወይም እገዳ ማውጣት ካስፈለገ በተገኘው መረጃ መሰረት ምክሮችን ያቀርባሉ። እያንዳንዱ ሰው ወቅታዊ እገዳዎች ማወቅ እንዳለበት በድረገጽ www.australia.gov.au ላይ ማየት።

የተሳሳተ መረጃ: እያንዳንዱ ሰው ምርመራ ካካሄደ የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ይቆማል

እውነቱ:  ምርመራ በማካሄድ የቫይረሱ ስርጭት አይቆምም።

ለኮቪድ/COVID-19 ቫይረስ መከላከልና መቆጣጠር መሰረታዊ ከሆኑት ጠቃሚ ነገሮች አንዱ የምርመራ ሂደትን በጊዜውና በትክክል በምርመራ ማጣራት ነው። በምርመራ ማጣራቱ የበሽታውን መተላለፊያ በትክክል ለመግለጽ፤ በሽታን ለማሳወቅና መቆጣጠሪያን በማነጋገር ተገቢ የሆነ የቫይረስ ስርጭት ቅነሳ በማድረግ ቁልፍ ሚና ይጫወታል።

ይሁን እንጂ በምርመራ የኮቪድ/COVID-19 ቫይረስ ከተገኘብዎት ችግር ላይ አይደሉም ወይም ለሌሎች ችግር አይፈጥርም ማለት አይደለም። በSARS-CoV-2 (ለኮቪድ/COVID-19 ምክንያት የሆነ ቫይረስ) ከተጋለጡ በኋላ በምርመራ የኮቪድ/COVID-19 ቫይረስ ላይገኝብዎት ይችላል፤ ነገር ግን ቀደም ሲል የበሽታ ምልክትን ያፈጥራሉ። ለዚህ ነው ጥሩ ጽዳት/ሃይጅን ማካሄድ፤ የአካል እርቀትን መጥበቅና ደህና ካልሆኑ እቤት መቆየቱ ጠቃሚ የሆነው። እነዚህ ድርጊቶች ከታቀደ ምርመራ ማካሄድ ጋር በጋራሆኖ ለኮቪድ/COVID-19 ስርጭትና ሌላ ተላላፊ በሽታዎች ስርጭት ለመከላከ እንደሚረዳ ታዲያ በአውስትራሊያ ጤና ጥበቃ አሰራር ዘዴ ላይ ያለን ጥያቄ ይቀንሰዋል።   

በቁጥር እየጨመረ ባለው ጕዳይና ወረርሽኝ በክልሉ ውስጥ ለሚፈለገው በወረሽኝ ቁጥጥርና ቀጣይ በሆነ ላቦራቶሪና የምርመራ ቦታ አቅም መካከል ትክክለኛ ሚዛናዊ የሆነ ጥንቃቄ የተሞላበት ምርመራ ለመካሄድ በታቀደው ላይ የህዝባዊ ጤና ጥበቃ ቁጥጥር ስኬታማ ውጤት አሳይቷል።  

የአውስትራሊያኖች በሰፊው ምርመራ ማካሄዱ የሚያሳየው ምንም የበሽታ ምልክት (የማይታይ ቫይረስ ተሸካሚ) እንደሌለ በመሆኑ በጣም ተስፋ ያስቆርጣል። ይህ የምርመራ ዘይቤ በተላላፊ በሽታ መልኩ ወይም ዋጋ በማያስከፍል የተላላፊ በሽታን ለመለየት አቀራረብ ይሆናል። በተወሰኑ የበሽታ ቁጥጥርና የመኖር ጉዳይ ላይ ምልክቱ ለማይታይ የምርመራ ተግባር ላይ የአውስትራሊያ መንግሥት ይቀበለዋል። በዚህ ይዘት ላይ የሚካተት የወረርሽኝ ቅንጅት፤ ከፍተኛ የመተላለፍ ችግር ላለባቸው ህዝቦች የችግሩን አካባቢ ለመቀነስ፤ በከፍተኛ የቫይረስ መጋለጥ ችግር ላይ ላሉ ህዝቦች እና በከፍተኛ የመተላለፍ ሁኔታ ላይ ላሉትና ብክለት ከተከሰተ ለከፍተኛ የበሽታ ችግር በቀላሉ ለሚጋለጡት ይሆናል።

የምርመራ አሰራሮች፤ ማለት በምርመራ ምልክት ለማያሳዩ ሰዎች በሥራ ቦታ ላይ የማጣሪያ ፕሮግራሞችን፤ አስፈላጊ ከሆነ የህዝባዊ ጤና ጥበቃ ባለሥልጣናትና ከላቦራቶሪ ዳሬክተሮች ጋር መማክርትን ማዳበር ያካተትን ቀጣይ እንዲሆን የአውስትራሊያ መንግሥት በቀጣይነት ይመክራል። ይህም በጣም ትክክለኛና ጥሩ የሆነ አቀራረብ በተቀጣሪዎች ላይ እንዲኖር ለማረጋገጥ ነው። በምርመራ ምልክት በማይገኝበት የተሰራጨ ቫይረስ በአውስትራሊያ የመንግሥት ሃላፊነት ለበለጠ መረጃ እባክዎ በድረገጽ Department of Health website ላይ ማየት።  

የተሳሳተ መረጃ: ለምርመራ የተዘጋጁ እቃዎች ትክክለኛ አይደሉም

እውነቱ:  አውስትራሊያ ውስጥ የኮቪድ/COVID-19 ምርመራዎች በጣም ትክክለኛ ናቸው። በአውስትራሊያ ውስጥ የምርመራ ዘዴዎች በሙሉ ለቅድመ ሁኔታዎች በማካተት የጸደቁ ናቸው። በተራፒቲክ ጉድስ አድሚኒስትሬሽን (TGA) አስተዳደር በቅርበት መቆጣጠሩን ይቀጥላሉ እንዲሁም በጥራት ባለው ኢንሹራንስ ዋስትና ፕሮግራሞች በኩል መሳተፉ ግዴታ እንደሆነ እና በተለይ ለ SARS-CoV-2 (ለኮቪድ/COVID-19 ምክንያት የሆነ ቫይረስ) እንዲዳብር አድርጓል።

በአውስትራሊያ ውስጥ በተለያየ እውቀት ባለው መርበብ (PCR) የላቦራቶሪ ምርመራ ግኝት መሰረት ባደረገ ወርቃማ እርምጃን ተጠቅሞ በስውነትዎ ውስጥ ያለን የማይድን በሽታ SARS-CoV-2 ተላላፊ በሽታ ለማጣራት እንዲሁም ምርመራን ለማካሄድ ከመተንፈሻ ናሙና መሰድ ያስፈልጋል። PCR ምርመራዎች በጣም ስሜት የሚነኩና አነስተኛ የጀነቲክ/ዘር ክፍልን በማሳየት በተለይ ለ SARS-CoV-2 በመተንፈሻ ውስጥ ናሙና ይወሰዳል።

በአውስትራሊያ አዲስ ለሆነ ማንኛውም ምርመራ ጥራቱንና ታማኝነት ያለው ውጤትና ህጋዊነት እንዲኖረው ለማረጋገጥ በ TGA በኩል በጣም ጥንቃቄ የተሞላበት ግምገማ እንዲደረግ ይፈለጋል። በአውስትራሊያ ምዝገባ የተራፒቲክ ጉድስ አድሚኒስትሬሽን (TGA) የተካተት እስከ ዛሬ ድረስ ላለው መረጃ በ(TGA) ድረገጽ: www.tga.gov.au/covid-19-test-kits-included-artg-legal-supply-australia ላይ ገብቶ ማየት።

የተሳሳተ መረጃ: ኮሮና ቫይረስ ለቀልድ ማታለል ነው

እውነቱ: ኮቪድ/COVID-19 በኮሮና ቫይረስ (SARS-CoV-2) የሚፈጠር ሲሆን ይህም የታላቅ ቫይረስ ቤተሰብ አካል እንደሆነና በሁለቱም በሰዎችና እንስሳት ላይ የመተንፈስ በሽታን ሊያስከትል ይችላል። እነዚህ የበሽታ ብክለቶች ከመደበኛ ጕንፋን እስከ በጣም ከባድ ህማም እስከመፍጠር ሊለያይ ይችላል። የኮቪድ/ COVID-19 ቫይረስ የሚሰራጨው በሰዎች መካከል በሚወጣ ጠብታ እና ቦታዎችን በመነካካት ይሆናል።

በአውስትራሊያ ውስጥ በፐተር ዶሀርትይ ተቋም/ Peter Doherty Institute ለተላላፊ በሽታና የበሽታ መቋቋም አቅም ባለው የቪክቶሪያ ተላላፊ በሽታዎች መላኪያ ላቦራቶሪ (VIDRL) ከቻይና ውጭ የSARS-CoV-2 ለመለየት የመጀመሪያው ላቦራቶሪ ነበር። VIDRL የተገለለን ቫይረስ ከሌላ የአውስትራሊያ ላቦራቶሪዎች፤ ከዓለም ጤና ጥበቃ ድርጅትና ሌሎች አገሮች ጋር በጋራ በመጠቀም ለኮቪድ/ COVID-19 ቫይረስ ምርመራዎች ማሻሻል፤ ማረጋገጥና የምርመራ ውጤቶችን ማግኘት እንዲቻል ነው።

SARS-CoV-2 ቫይረስን ለመለየትና ለማሳወቅ በህዝባዊና በግል የበሽታ ላቦራቶሪዎች ባሉት ትክክለኛ አቅም ባላቸው ተቀባይነት ያገኙ ኤክስፐርቶች አሰራር መርበብ በኩል ድጋፍ በማግኘት አውስትራሊያ እድለኛ ነች። የእነዚህ ላቦራቶሪዎች ችሎታ አቅም ለምርመራ አቅም መጠን በማመዛዘን ለዚህ ወረርሽኝ በለላ አገሮች የታየውን ወረርሽኝ መጠን በአውስትራሊያ እንዳይፈጠር የቫረስ መስፋፋት መጠን ለመቀየርና ለማስወገድ ነው። ከኮቪድ/COVID-19 ቫይረስ ጋር ስላሉ እና ከበሽታው ስለሞቱት ቁጥር ሰዎች መረጃ በአውስትራሊያና በሞላው ዓለም ተሰብስቧል። በየቀኑ ጥሬ መረጃ በጽሁፍ የሚቀርበው በ Australian Department of Health ይሆናል።

የተሳሳተ መረጃ: የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብሎች ጥሩ እንዳልሆ እና/ወይም ደህንነት የላቸውም።

እውነቱ: ጭንብሎችን ከሌላ ማስጠንቀቂያዎች ጋር ሲጠቀም፤ እንደ ጥሩ ጽዳት/ሃይጂን፤ የአካል እርቀትን መጠበቅና ደህና ካልሆኑ እቤትዎ መቆየትና ምርመራ ማካሄዱ ለኮቪድ/COVID-19 ቫይረስ ስርጭት ይረዳል።

እንደ አብዛኛው የትንፋሽ ቫይረሶች፤ የ SARS-CoV-2 (ለኮቪድ/COVID-19 ምክንያት የሆነ ቫይረስ) በአብዛኛው ቫይረሱ የሚሰራጨው ቫይረስ ባለበት ጠብታዎች በኩል ሲሆን፤ ይህም በቫይረሱ የተበከለ ሰው ሲናገር፤ በሚስልበት ወይም በሚያስነጥበት ጊዜ ቫይረሱ ይሰራጫል ነው። እንዲሁም በተበከሉ ስፍራዎች በኩል ስርጭቱ ሊካሄድ ይችላል። የትንፋሽ ብክለት ቫይረስ ባለበት ሰው፤ ይህም የኮቪድ/ COVID-19 በሽታ ምልክት ያለበት ወይም የሌለብትን ያካተተ ሌሎችን ከቫይረስ ለመከላከል የተበከለን ትንፋሽ ጠብታዎች ስርጭት መቀነስ ይሆናል። የጤና እና እንክብካቤ አቅራቢ ሰራተኞች ኮቪድን/ COVID-19 ያካተተ፤ ከትንፋሽ ብክለት ጋር ያለን ሰው በእርቀት መከላከል ካልቻሉ ጭምብሎችን ይጠቀማሉ።

ለኮቪድ/ኮቪድን/ COVID-19 ቫይረስ ስርጭት ለማዳከም ጭምብል ማጥለቅ አንድ እርምጃ ብቻ እንደሆነና ሌላ ጥንቃቄ እንደማይተካው ነው። ጥሩ የእጅና መተንፈሻ ጽዳት/ሃይጅን፤ የአካል እርቀትን በመጠበቅ መቀጠሉ እና ደህና ካልሆኑ እቤት መቆየትና ምርመራ ማካሄዱ አስፈላጊ ነው።

የፊት መሸፈኛ ጭንብል በማድረግ ደህንነት እንደሌለው ወይም ወደ ኦክስጅን አየር እጥረት እንደሚያስከትል የሚያሳይ መረጃ የለም። የጤና እንክብካቤ አቅራቢዎች ያለነዚህ ችግሮች ለብዙ ዓመታት ለረጅም ጊዜ ጭንብል አድርገዋል።

 

በአውስትራሊያ መንግሥት ለኮቪድ// COVID-19 ቫይረስ ምላሽ ስላለው ቁልፍ የሆነ መሻሻል ለማወቅ መረጃ በዚህ ድረገጽ በተደጋጋሚ ይቀርባል።

እንዲሁም SBS ስለ ኮቪድ/COVID-19 የተለያየ መረጃ በራስዎ ቁንቋ እንዳለው ነው። እንዲሁም የመንግሥት መረጃን ለመተርጎም የሞባይል ስልክ አፕስ/apps እና ብራውዘር ኤክስተንሽን/ browser extensions መጠቀም ይችላሉ። ለርስዎ ፍላጎት የሚያሟላ አንዱን መፈለግ።

ተጨማሪ መረጃ በእንግሊዝኛ ለማውጣት በድረገጽ፡ www.australia.gov.au ላይ ገብቶ ማየት።