ጤና

ህይወትን ማዳንንና በአውስትራሊያ ውስጥ ለኮሮና ቫይረስ/coronavirus ስርጭት ቅነሳ መርዳት

በቤት ውስጥ መቆየት

 • ማድረግ ከሌለብዎት በስተቀር ከቤት ውስጥ አለመውጣት።

 • ጠቃሚ ላልሆነ ጉዳይና ሥራ ተብሎ ከቤትዎ መውጣትን ማስወገድ።

 • ወደ ቤትዎ ቤተሰብ ወይም ጓደኞች እንዲመጡ አለመጋበዝ።

 • ከዚህ በታች ላለ ካልሆነ በስተቀር ቤትዎ ውስጥ መቆየት:

  • ወደ ሥራ ወይም ትምህርት መሄድ (በቤትዎ ውስጥ ማካሄድ ካልቻሉ)

  • ጠቃሚ ለሆኑ አቅርበቶች ማለት እንደ የምግብ ቆሳቁስ ግሮሰሪ ለመግዛት (ሳይዘገዩ ወደ ቤት መመለስ)

  • በጎረቤታሞች ክልል ላይ ግላዊ አካል እንቅስቃሴ ለማድረግ ለብቻዎ ወይም ከሌላ አንድ ሰው ጋር ከቤት ወጥቶ መሄድ

  • በህክምና ቀጠሮ ለመገኘት ወይም ለርህራሄያዊ ጉብኝት ለመገኘት ካልሆነ።

 • የህክምና አገልግሎቶች፤ ሱፐርማርከቶች፤ ባንኮች፤ ነዳጅ ማደያዎች፤ ፖስታ ቤት እና ወደ ቤት ማድረሻ አገልግሎቶች ክፍት ሆነው ይቆያሉ።

ደህንነትን መጠበቅ

 • ሁልጊዜ ጥሩ ለጤንነት ሃይጅን፤ እጅን ለ20 ሰኮንዶች የሚሆን በሳሙና እና በውሃ መታጠብ እንዲሁም በሚስሉበት ጊዜ መሸፈን፤ የርስዎን ዓይኖች፤ አፍንጫ እና አፍ መንካትን ማስወገድ።

 • ከቤትዎ ውጭ በሚሆኑበት ጊዜ የማሕበራዊ ግንኙነት እርቀት ቢያንስ 1.5 ሜትር ማድረግ።

 • በአካል ግንኙነት ሰላምታ እንደ በእጅ መጨባበጥ፤ መተቃቀፍ እና መሳሳምን ማስወገድ።

 • ከጥሬ ገንዘብ መጠቀም ባሻገር በካርድ መንካት ማካሄድ።

 • ጸጥ ባለ ጊዜ መጓዝ እንጂ በተጨናነቀ ጊዜ ማስወገድ።

 • ደህንነት ያለው መረጃ ማግኘት – የታመኑ ህጋዊ መረጃን ብቻ መጠቀም። የኮሮና ቫይረስ አውስትራሊያ ሞባይል ፎን አፕ/Coronavirus Australia mobile phone app, በመጫን ለኮሮና ቫይረስ አውስትራሊያ ዋትስአፕ አገልግሎት/Coronavirus Australia WhatsApp service መመዝገብና ወቅታዊ መረጃን ለማግኘት በድረገጽ፡ www.australia.gov.au ላይ ማየት።

ግንኙነትን መቀጠል

 • በስልክ ወይም በመስመር አድርጎ ስለ ቤተሰብና ጓደኞች ማጣራት።

 • ለሽማግሌ ዘመዶች እና በችግር ላይ ላሉ ሰዎች ጠቃሚ የሆኑትን እቃዎች በቤት ደጃፍ ላይ ማድረስ።

 • ቁልፍ የሆኑ ፈቃደኛ ድርጅቶች እና በጎ አድራጊ ድርጅቶች አገልግሎት በጣም ለሚያስፈልጋቸው ሰዎች አሁንም አገልግሎቶችን ማቅረብ ይችላሉ።

ስለ ጤና መረጃ

በኮሮና ቫይረስ/coronavirus ምልክቶች የሚካተት:

 • ትኵሳት

 • መሳል

 • የጕሮሮ ህመም

 • ከፍተኛ ድካም

 • የትንፋሽ እጥረት

ከታመሙና ምናልባች ኮሮና ቫይረስ/coronavirus አለብኝ ካሉ የህክምና እርዳታ ያስፈልግዎታል።
መረጃ ለማግኘት ለኮሮና ቫይረስ እርዳታ መስመር/National Coronavirus Helpline መደወል ይችላሉ። የትርጉምና

አስተርጓሚ አገልግሎትን ከፈለጉ በስልክ 131 450 አድርጎ መደወል።
ከፍተኛ የህመም ምልክት እንደ የመተንፈስ ችግር ያለ ካለብዎት ለአስቸኳይ የሆነ እርዳታ በስልክ 000 አድርጎ መደወል።

ለሰዎች ደህንነት ጥበቃ ለመርዳትና በማህበረሰቡ የሚከሰትን ችግር ለመቀነስ ሲባል በጤና ጥበቃ መምሪያ ድረገጽ ላይ የተለያዩ መረጃዎች ከእንግሊዝኛ ቋንቋ ባሻገር በሌላ ቋንቋዎች ቀርቧል።