ቪዛዎች እና ድንበር

ለጕዞ እገዳ/ክልከላ

ለአውስትራሊያ ዜጎች ላልሆኑት እና ነዋሪዎች ላልሆኑት በሙሉ ወደ አውስትራሊያ እንዳይገቡ መከላከያ የጉዞ እገዳ ተቀምጧል።

ከጉዞ እገዳ ነጻ በሆኑ ሰዎች ላይ የሚካተት የአውስትራሊያ ዜጎችና ቋሚ መኖሪያ ፈቃድ ላላቸው የቅርብ ቤተሰብ አባላት እንደ ባል/ሚስት፤ ለአካለ መጠን ላልደረሱ ጥገኞች፤ ህጋዊ ለሆኑ መጉዚቶች እና ህጋዊ ያልሆኑ ጥንዶችን ያካትታል። ሁሉም ተጓዥ ወደ አውስትራሊያ ከደረሱ በኋላ ለ 14 ቀናት እስኪጠናቀቅ ለብቻ መገለያ ቦታ ላይ መቆየት ያስፈልጋል።

ለጊዜያዊ ቪዛ ለያዙ መረጃ

አውስትራሊያ ውስጥ ከተፈቀደላቸው ቀን በላይ መቆየት ለሚፈልጉ ቪዛ ላላቸው ታዲያ አሁን ያላቸው ቪዛ እንዲራዘምላቸው ማመልከት አለባቸው። ቪዛ ያላቸው በነሱ ሁኔታ ላይ ተስማሚ የሆነ አዲስ ቪዛ ለማግኘት ያለውን ምርጫ መፈለግ እና ለዚ ማመልከቻ ማስገባት ስለመቻላቸው ማጣራት አለባቸው።

ስለ ጉዞ እገዳ/ክልከላ እና ቪዛ የበለጠ መረጃ ለማግኘት በድረገጽ፡ covid19.homeaffairs.gov.au ላይ ገብቶ ማየት