ዘረኝነት ተቀባይነት የለውም

በዘር ለይቶ ኣድልዎ ፈጠራ፤ ጥቃት ወይም ጥላቻቻ ደርሶብዎት ወይም አይተው ከሆነ ዝም አለማለት፤ አውጥቶ መናገር ነው።

በዘረኝነት ባህሪ ጥቃት ተበዳይ ከሆኑ

 • ከብጥብጥ ጋር የስድብ ወረራ ወይም ማስፈራራት ከደረሰብዎት ለፖሊስ ማነጋገር።  
  • በድንገተኛ ችግር ጊዜ ወይም ለህይወት የሚያስፈራ ሁኔታ ላይ በሶስት ዜሮ (000) አድርጎ ደውሎ ለፖሊስ መጠየቅ።
  • የፖሊስ እርዳታ ከፈለጉ፤ ነገር ግን ቀጥተኛ ያልሆነ አደጋ ከሌለ፤ ለፖሊስ እርዳታ መስመር በስልክ (131 444) መደወል።  
 • ብጥብጥ ሁከት ካልተጨመረበት በራስዎ ለማካሄድ ደህንነቱ የተጠበቀ ከሆነ በቀጥታ ከሰውየው ወይም ተሳትፎ ካደረገ ሰው ጋር ስለሁኔታ መደራደር ይፈልጉ ይሆናል።
 • በቀጥታ ተነጋግሮ ሁኔታውን መፍታት ካልተቻለ ወይም ይህን ለማድረግ ምቹነት ካልተሰማዎት ቅሬታዎን ለአውስትራሊያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (AHRC) ማቅረብ ይችላሉ። .
  • ቅሬታዎን ከ AHRC ጋር ለማስገባት፤ ድረገጽ፤ www.humanrights.gov.au/complaints ወይም ለአውስትራሊያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (AHRC) አገር አቀፍ መረጃ አገልግሎቶች በስልክ 1300 656 419 ወይም በቁጥር 02 9284 9888 መደወል።  

የተመልካቾች ሥልጣን

አንጻራዊ ለሆነ ዘረኝነት ንግግር መስካሪ ሰዎች፤ ሰውየው እርዳት ፈላጊ መሆኑ ስለሚሰማቸው ታዲያ ይህን ሰው ባለበት የዘረኝነት ባህሪ ዘረኛ ሊያሰኘው ይችላል። እራስዎን በችግር ውስጥ አለማስገባት። ነገር ግን ይህን ለማካሄድ ደህንነቱ የተጠበቀ ከሆን መናገርና ከተበዳዩ ጋር መቆም። ቀላል የምልክት ግንኙነት ማሳየትም ታላቅ ተጽእኖ ሊያሳድር ይችላል።

የዘረኝነት ባህሪ ካዩ ማድረግ የሚችሉት:

 • ድምጽን ከፍ አድርጎ መናገር — እንደ ዘረኝነት ስለሚባል፤ ታዲያ ወንጀለኛው ተቀባይነት እንደሌለው እንዲያውቅ ማድረግ
 • ተበዳይን መደገፍ — ችግር ውስጥ ካለው ሰው ጎን መቆምና ስለደህንነታቸው መጠየቅ    
 • ማስረጃ መውሰድ — በስልክዎ ላይ የተፈጠረውን አድራጎች ችግር ሪኮርድ ማድረግ፤ የወንጀለኛውን ፎቶ መውሰድና ለባለስልጣኖች ሪፖርት ማድረድ

የአውስትራሊያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (AHRC) ለተመልካቾች ምክሮችን አለው በድረገጽ፡ https://itstopswithme.humanrights.gov.au/respond-racism ገብቶ ማየት።

በዘረኝነት አድልዎ ፈጠራ እና የርስዎ መብቶች

የአንድን ሰው ዘር፤ ቀለም፤ የመጣበትን አገር ወይም የአንድን ግለሰብ ወይም ቡድን የመጣበትን ጎሳ መነሻ አድርጎ በአደባባይ ህዝብ ፊት የሆነ ነገር ማድረግ ማለት እንደ ማናደድ፤ መሳደብ፤ ማዋረድ ወይም ማስፈራራት አውስትራሊያ ውስጥ ህገ-ወጥነት ይሆናል። የዚህ ዓይነት ባህሪ እንደ ዘረኝነት ጥላቻ ይመደባል።

ለምሳሌ፡ በዘረኝነት ጥላቻ ሊካተት የሚችል:

 • በኢንተርኔት አድርጎ ለዘረኝነት የማናደጃ ነገሮች፤ በዚህ ኢንተርኔት የሚካተት እፎሩምስ/eforums፤ ብሎግስ/blogs ማሕበራዊ መገናኛ አውታር እና በቪዲዮ ማሳተፊያ ቦታዎች
 • በጋዜጣ፤ መጽሄት፤ ወይም በሌላ ጽሁፋዊ ህትመት እንደ አጭር ጹሁፍ ወይም በራሪ ወረቀት አድርጎ ዘረኝነትን በሚያናድድ አስተያየት ወይም ገጽታን ማውጣት
 • ህዝብ በተሰበሰበት ላይ ዘረኝነትን የሚያናድድ ንግግር
 • በህዝባዊ ስፍራ እንደ ሱቅ፤ መገበያያ ቦታ፤ ሥራ ቦታ፤ መናፈሻ ቦታ፤ በህዝብ ማጓጓዣ ወይም በትምህርት ቤት ላይ ዘረኝነትን የሚዘልፍ አስተያየት
 • በስፖርት ድርጊቶች ላይ ዘረኝነትን የሚሳደብ ዘለፋ አስተያየት በተጫዋቾች፤ በተመልካቾች፤ አሰልጣጮች ወይም ሀላፊዎች ይሆናል።

የህጉ ዓላማ በንግግር ግንኙነት ነጻ ሆኖ የመናገር መብት ግጭት ሚዛናዊ ለማድረግ (‘የንግግር ነጻነት’) እና ከዘረኝነት ጥላቻ ነጻ በሆነ የመኖር መብት ነው። አንዳንድ ድርጊቶች ህገወጥ ሊሆኑ የሚችሉት “ሆነ ተብሎና እያወቁ” ካደረጉት ነው።

የዘረኝነት አድልወ ፈጠራ የሚከሰተው በተመሳሳይ ካሉት ሰዎች ዘር፤ ቀለም፤ የትውልድ ዘር፤ የመጣበት አገር ወይም ጎሳ ወይም የኢሚግራንት መጤን ሁኔታ ምክንያት አድርጎ አንድን ሰው ነጥሎ ያላግባብ ዝቅተኛ የሆነ መስተንግዶ ከደረሰበት ሲሆን፤ ይህም ሰዎች ባላቸው ዘር ጎሳ አመጣት ወይም የቆዳ ቀለም ምክንያት አድርጎ እንደ ቤት ለማከራየት እምቢ ማለት ይሆናል።

እንዲሁም የዘረኝነት አድልወ ፈጠራ የሚፈጠረው ለሁሉም ተመሳሳይ የሆነ ደንብ ወይም ፖሊሲ ካለ ነገር ግን ሰዎች ባላቸው ዘር፤ ቀለም፤ የትውልድ ዘር፤ የመጣበት አገር ወይም ጎሳ ወይም የኢሚግራንት መጤን ሁኔታ ምክንያት አድርጎ እንደ ኩባንያው ለተቀጣሪዎች በሥራ ቦታ ላይ ባርኔጣ ወይም የጭንቅላት የሚጠለቅ አታድርጉ ማለት ታዲያ በአንዳንድ ዘር/ጎሳ ለመጡት ሰዎች አግባብ ያልሆነ ችግር ሊፈጠር ይችላል።

የዘረኝነት አድልወ ፈጠራ ወይም ጥላቻ ከደረሰብዎት ቅሬታ ወደ አውስትራሊያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (AHRC) ማቅረብ ይችላሉ። ቅሬታው ቀላል፤ ያለክፍያ በነጻና ተለዋዋጭ ይሆናል።  

በአውስትራሊያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (AHRC) የቅሬታ ማመልከቻ ለማስገባት በድረገጽ፡ www.humanrights.gov.au/complaints ላይ ገብቶ ማየት።

አገር አቀፍ መረጃ አገልግሎት

የአውስትራሊያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን የአገር አቀፍ መረጃ አገልግሎት (NIS) ስለተለያዩ ሰብአዊ መብቶችና አድልወ ፈጠራ ጕዳይ በተመለከተ ለግለሰቦች፤ ድርጅቶችና ቀጣሪዎች መረጃና ወደሚመለከተው የመላክ እርዳታን ያቀርባል። ይህ አገልግሎት በሚስጢራዊና ያለክፍያ በነጻ ይቀርባል።

የ NIS ማድረግ የሚችለው:

 • በፈዴራል ሰብአዊ መብቶችና በጸረ-አድልወ ፈጠራ ህግ መሰረት ስላለዎት መብቶችና ሃላፊነቶች መረጃ ያቀርብልዎታል
 • ቅሬታዎን ወደ ኮሚሽኑ ለማስገባት መቻል ወይም አለመቻል ወይም በርስዎ ሁኔታ ላይ እንዴት ህጉ ተግባራዊ ሊሆን እንደሚችል ከርስዎ ጋር መወያየት
 • እንዴት ቅሬታ ማስገባት፤ ለቅሬታው ምላሽ መስጠት ስለሚችሉ መረጃ መስጠት ወይም ለየት ባሉት አድልወ ፈጠራ ጉዳዮች ላይ ስለመደራደር መረጃ ይሰጥዎታል
 • እርስዎን ሊረዳ ወደሚችል ሌላ ድርጅት መላክ

እባክዎ ያስተውሉ የ NIS ህጋዊ ለሆነ ምክር ማቅረብ አይችልም።

ለ NIS ማነጋገር የሚችሉት:

የትርጉምና አስተርጓሚ አገልግሎት

የትርጉምና አስተርጓሚ አገልግሎት (TIS National) እንግሊዝኛ ለማይናገሩ ሰዎች የአስተርጓሚ አገልግሎት ነው። አብዛኛው በትርጉምና አስተርጓሚ (TIS National) የሚቀርቡ አገልግሎቶች እንግሊዝኛ ለማይናገሩ ያለክፍያ በነጻ ይሆናል።

መማክርትና የአእምሮ ጤና ደህንነት

በተለይ በCOVID-19 ቫይረስ ወረርሽን ሳቢያ ለተቸገሩ ሰዎች ለመርዳት ተብሎ የወጣ አዲስ 24/7 በቀን ለ24 ሰዓታት በሳምንት 7 ቀናት የድጋፍ አገልግሎት እንደሚቀርብ ይህም አውስትራሊያኖች በሙሉ ያለክፍያ በነጻ ይሆናል።

የድጋፍ አገልግሎት ሊገኝ የሚችለው በድረገጽ፡ https://coronavirus.beyondblue.org.au/ በኩል ነው።

ለግለሰብ ኪሳራ ችግር እና ለአእምሮ ጤና ጥበቃ ድጋፍ አገልግሎቶች ለበዮድ ብሉ/Beyond Blue በስልክ 1800 512 348 ወይም ህይወት መስመር/Lifeline በስልክ 13 11 14 አድርጎ በማንኛውም ጊዜ ማነጋገር ይችላሉ።

የህጻናት እርዳታ መስመር/Kids Helpline አገልግሎት የሚቀርበው እድሚያቸው ከ5 እስከ 25 ዓመት ለሆኑ ለታዳጊ ወጣቶች ያለክፍያ በነጻ ይሰጣል። ህጻናት፤ ታዳጊዎችና ጐረምሳዎች በስልክ 1800 551 800 አድርጎ በማንኛውም ጊዜ ማነጋገር ይችላሉ።